Monday, September 10, 2018


Image result for breast caImage result for breast ca
የጡት ካንሰር ምንነት፤ ስርጭት ፤መንስኤ ፤ምልክት እና ህክምና
የበሽታው ምንነት
የጡት ካንሰር ማለት በጡት ዉስጥ ካሉት የወተት ማምረቻ እና ማስተላለፊያ ትንንሽ የጡት ክፍሎች የሚነሳ የካንሰር አይነት ሲሆን በጡት ዉስጥ ያሉት ህዋሶች ያለአግባብ ከተፈጥሮአዊ የህዋስ ርቢ ህግ ዉጭ በሚያደርጉት መባዛት የሚከሰት ነዉ:: ይህ የካንሰር አይነት በሴቶች ላይ በአንደኝነት የሚከሰት እና ከሌሎች ካንሰር አንጻር ሲታይ ሁለተኛ ገዳይ የሆነ የካንሰር አይነት ነዉ::
የበሽታዉ ስርጭት
የጡት ካንሰር ከስምንት ሴቶች የህይወት ዘመን ዉስጥ በአንዷ ሴት ላይ ሊከሰት የሚችል የካንሰር አይነት ነዉ:: በፐርሰንት ስናየው ደግሞ ወደ 12% አካባቢ የሚደርስ የበሽታ ስርጭት አለዉ:: በዚህ በሃገራችን በኢትዮጲያ እንኳ ብዙ ሴቶች ቶሎ ወደ ሆስፒታል ባለመሄዳቸው  እና በሽታው አስከፊ ደረጃ ከደረሰ በኋላ ወደ ጤና ተቋማት በመሄዳቸው ብዙ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል::
የጡት ካንሰር መንስኤዎች
Ø  የእድሜ መግፋት
Ø  BRCA1/BRCA2 ዘረ መል ባህርይ መቀየር
Ø  እናት ወይም እህት በጡት ካንሰር መጠቃት (በዘር መጠቃት)
Ø  ከዚህ በፊት ሌላኛዉ ጡት በካንሰር መጠቃት
Ø  ደረት አካባቢ ላይ ለራጅ ጨረር መጋለጥ
Ø  የመጀመሪያ ልጅን ከ30 አመት በላይ ከሆኑ በኋላ መዉለድ
Ø  የሚዋጠዉን የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን መዉሰድ
Ø  ያለቅጥ የሰዉነት ዉፍረት
Ø  ምንም ልጅ አለመዉለድ
Ø  የመጀመሪያ የወር አበባ ከ12 አመት በፊት መከሰት
Ø  የወር አበባ ከ55 አመት በላይ መቆየት
Ø  ከዚህ በፊት በማህጸን ካንሰር ተጠቂ መሆን

የበሽታው ምልክቶች

አብዛኛው ጊዜ የጡት ካንሰር ወደ ብብት የሚጠጋው የላይኛው የጡት ክፍል አካባቢ ላይ ይከሰታል:: ምልክቶቹም የሚከተሉት ናቸዉ:_

v  በጣም ጠንካራ ጠጣር የማይነቃነቅ የጡት እብጠት
v  የጡት ጫፍ ወደ ዉስጥ መግባት
v  ከጡት ጫፍ ደም መፍሰስ
v  ከቆዳ ጋር የተያያዘ የጡት እብጠት
v  ከደረት ጋር የተያያዘ የጡት እብጠት
v  የጡት መቁሰል እና መፍረስ
v  ብብት ዉስጥ ጠጣር እብጠቶች መታየት(lymph node enlargement)
v  ካንሰሩ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍሎች የተዛመተ ከሆነ ደግሞ የጀርባ አጥንት ህመም የአይን ቢጫ መሆን እና ሳል ሊከሰት ይችላል::

የጡት ካንሰር አስከፊ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ በካንሰሩ ከሚከሰቱ ሌሎች ችግሮች እና ሞት እራስን በጣም መከካከል ይቻላል። ስለዚህ ማንኛዉም ሴቶች ሻወር ቤት ሲገቡ የራሳቸዉን ጡት በመዳሰስ የጡት እብጠትን ቶሎ በማወቅ እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ዶክተር ማማከር ተገቢ ነው።

ለጡት ካንሰር የሚሰጡ ህክምናዎች

የጡት ካንሰር የክምና አይነቶች የሚወሰነው እንደየእብጠቱ እና እንደየደረጃዉ የሚለያይ ሲሆን በአጠቃላይ ግን ህክምናዎች በ3 ይከፈላሉ። እነሱም፦

ü  የቀዶ ጥገና ህክምና (surgery)
ü  የጨረር ህክምና (radiotherapy)
ü  በመድሃኒት የሚታከም (medical therapy)
ናቸው።
ማንኛዉንም የጤና ጥያቄዎችን በኮሜንት ቦክስ መጠየቅ ይቻላል።

Follower በመሆን ለሎችንም የጤና ምክሮች ያግኙ
 እናመሰግናለን።


No comments:

Post a Comment